ባለስልጣኑ "ህገወጥ እርድና እንስሳት ዝዉዉርን በህብረተሰብ ተሳትፎ እንቀንሳለን!" በሚል መሪ ቃል በከተማ ያስጀመረውን የህብረተሰብ ውይይት በሁሉም ወረዳዎች እየተካሄደ ነው
ባለስልጣኑ "ህገወጥ እርድና እንስሳት ዝዉዉርን በህብረተሰብ ተሳትፎ እንቀንሳለን!" በሚል መሪ ቃል በከተማ ያስጀመረውን የህብረተሰብ ውይይት በሁሉም ወረዳዎች እየተካሄደ ነው
ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤቱ አስተባባሪነት በደንብ ቁጥር 150/2015 ህገወጥ እርድና የእንስሳት ዝዉዉርን በሚመለከት ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት ንቅናቄ መድረክ አካሄደ ።
በመድረኩም የሀይማኖት አባቶች፣ የሆቴል ባለቤቶች፣ የማህበረሰብ ተወካዮች የጽዳት ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የሀይማኖት አባቶች መርሃ ግብሩን በፀሎት አስጀምረዋል።
የዉይይቱን የመነሻ ሰነድ የጽህፈት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር ደሳለኝ ሌንጮ ያቀረቡ ሲሆን ህገወጥ እርድ የከተማዋን እድገትና ውበት በመቀነስ ለሀገር ኢኮኖሚ እና ለማህበረሰቡ ጤና ጠንቅ መሆኑን አስረድተዋል።
ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ሰፊ ዉይይት ያደረጉ ሲሆን በዉይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች መድረኩን የመሩት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር ደሳለኝ እና የወረዳው ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሙላት ንጉሴ፣ የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም መኮነን ህገወጥ እርድ በማህበረሰቡ እና በሀገር የሚያሳድረዉን ተጽዕኖ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመድረኩ ህገወጥ እርድን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ድርሻ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments