ባለስልጣኑ የ2018 ዓ.ም ህዳር ወር እቅድ አፈ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የ2018 ዓ.ም ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።

ባለስልጣኑ የ2018 ዓ.ም ህዳር ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገመገመ።

                       ታህሳስ 1/2018ዓ.ም
                            **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የህዳር ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የማዕከል ፣ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂድዋል።

በመድረኩ በህዳር ወር የተከናወኑ አበይት  ተግባራት ፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች ፣ የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት መስኮች የተመለከተውን ሪፖርት ያቀረቡት የባለስልጣኑ
ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ናቸው።

በሰነዱም የኦፊሰር ስምሪት የአሰራር ሁኔታ፣ የአመራርና የኦፊሰር የስነ-ምግባር ጥያቄዎች፣ የቅሬታ አቀባበልና አፈታት፣ የግንዛቤ አሰጣጥና የመጡ ለውጦች ላይ ግምገማ የማድረግ፣  የአገልግሎት አሰጣጥ እና ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር በሚሉ ነጥቦች ላይ በጥንካሬ የታዩትን በማንሳት ለሌሎቹ የተሞክሮ ማጋራትና በክፍተት ለታዩ  የመፍትሄ ሀሳቦችን በመስጠት ሰፊ ውይይት ተካሂድዋል።

በመጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ስ/አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከሪፖርቱ በመነሳት የተሻለ አፈጻጸም በታየባቸው የደንብ ጥሰቶች ላይ የበለጠ የተጠናከረ ስራ ሊሰራ እንደሚገባና ሌሎች በአፈጻጸም ክፍተት የታየባቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ተቋሙ የያዘውን ራዕይና ተልዕኮ ለመወጣት ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ በማስገንዘብና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩን አጠቃለዋል።

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments