የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፌደራል...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዩንቨርስቲ አዳይቱ ካምፓስ እየተሰጠ የሚገኘውን የስልጠና ሂደት የመስክ ምልከታ አደረጉ

የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዩንቨርስቲ አዳይቱ ካምፓስ እየተሰጠ የሚገኘውን የስልጠና ሂደት የመስክ ምልከታ አደረጉ

          ህዳር 30/2018 ዓ.ም
           **አፋር አዳይቱ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ አዳይቱ ካንፓስ ለክፍለ ከተማና ወረዳ ቡድን መሪዎች፣ሽፍት አስተባበሪዎች፣ ሽፍት መሪዎችና ኦፊሰሮች እየተሰጠ ያለውን የንድፈ ሀሳብና አካል ብቃት የስልጠና ሂደት ጉብኝትና የመስክ ምልከታ አደረጉ።

የጉብኙት ልዑኩን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ ባደረጉት ንግግር የስልጠናው ዋና አላማ አዲስ አበባ ከተማ ላይ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ የከተማዋ ልማትና ውበት ለማስጠበቅ በእውቀትና በአካል ብቃት የጎለበተ የሰው ሀይል በማስፈለጉ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም እስከ አሁን በተሰራው ስራ በተጨባጭ በከተማዋ የሚስተዋለው የደንብ መተላለፍ እየቀነሰ መምጣቱን ጠቅሰው በስልጣናው ያገኛችሁትን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በሀገር ፍቅር ስሜት ወደ ተግባር በመቀየር በሚሰጣችሁን ተልእኮ በሰብአዊነትና አገልጋይነትን መልካም ስነ-ምግባር በመላበስ ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ ለሰልጣኞቹ መልእክት አስተላልፈዋል።

በተጨማሪውም ይህ ስልጠና ተቋሙን ለማጠናከር በሚደረጉ የተቋም ግንባታ ስራዎች አይነተኛ ሚና እንዳለውና በቀጣይም በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ለመስራት ዝግጅት መደረጉን፣ የተቋሙን ተልእኮ የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አውስተዋል።

ከሰልጣኞቹ የሚነሱ ጥያቄዎችን ጨምሮ ሌሎች የስራ መመሪያዎች በቀጣይ  የማጠቃልያ ውይይት መድረክ  እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በጉብኝቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ፣ የባለስልጣኑ  የቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ታደሰ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ  የአመራር አቅም ግንባታ እና ስልጠና ማእከል ሀላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው እንዲሁም ሌሎች የሁለቱም ተቋም ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው በስልጠና ቆይታቸው ለስራቸው የሚጠቅም በርካታ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ከቅርብ ሀላፊ እና ከማህበረሰቡ ጋር ተግባቦትን የሚያጠናክሩ እውቀትና የአካል ብቃት ማጎልበቻ ስልጠና እንዳገኙ ገልፀዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments