የባለስልጣኑ የሦስተኛ ዙር የአካል ብቃትና እና...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የሦስተኛ ዙር የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣኝ አመራሮች እና ኦፊሰሮች አቀባበል ተደረገ

የባለስልጣኑ የሦስተኛ ዙር የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣኝ አመራሮች እና ኦፊሰሮች አቀባበል ተደረገ

             27/03/2018 ዓ.ም
               **ሰንዳፋ**     

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የሦስተኛ ዙር የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሰልጣኝ አመራሮች እና ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መድረሳቸው ተገለፀ።

ሰልጣኞቹ ወደ ማሰልጠኛው ሲደርሱ የባለስልጠኑ አመራሮ እና የስልጠና አስተባባሪዎች ከዩኒቨርስቲው አመራርና ማህበረሰብ ጋር በመሆን አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የአቅም ግንባታና የስልጠና ማዕከል መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸዉ ጋራ በመሆን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን አስጀምረዋል አስጀምረዋል።

በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ሥልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት  እንደሚቆይና በመግለፅ ሰልጣኞች ስልጠናው በዲሲፕሊን፣በንቃትና በብቃት እንዲከታተሉ መልዕክት ተላልፏል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments