ባለስልጣኑ ከሁለተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከሁለተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ

ባለስልጣኑ ከሁለተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ

           26/03/2018 ዓ.ም
             ** ሰንዳፋ**    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የአካልብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና የማጠቃለያ ውይይት የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት አካሂደዋል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋማችን በየጊዜው ራሱን የማዘመንና የማጠናከር ስራ የሚሰራው ከተማችን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ መዲና እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መቀመጫ በመሆኗ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ሰላምና ጸጥቷ የተጠበቀ ለነዋሪዎቿ እና ለእንግዶች ምቹ ጽዱ ማራኪ በማድረግ በስነምግባር የታነጸ ኦፊሰር በመገንባት የተሰጠንን ተልዕኮ በውጤት ለመወጣት መሆኑን ገልጸዋል ።

አቅማችንን በየጊዜው በማሻሻል ከባለድርሻና ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል እና ሰላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት የማስጠበቅ ከፍተኛ ስራ በደንብ ማስከበር መስራቱንና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

አክለውም ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን በሚገባ በማስተካከል ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ስነምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የከተማችን ፈጣን እድገት ያማከለ ወቅቱን ያዋጀ ስልጠናዎችን ለአመራሩና ኦፊሰሮች በመስጠት ተቋሙ በከተማው አስተዳደር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት በመፈጸም የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት እንዲቀንሱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም አመራርና ኦፊሰሩን ለማብቃት በየጊዜው ወቅቱን የጠበቀ ስልጠናዎች እየተዘጋጁ የሚሰጥ መሆኑን የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments