የደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ የበጎ...

image description
- In code inforcement    0

የደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ የበጎ ፈቃደኞች ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለፀ

የደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ የበጎ ፈቃደኞች ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለፀ

                  ህዳር  26/2018 ዓ.ም
                  **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን    ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከወረዳ እና ከክ/ከተማ ለተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው  የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን እንደገለፁት የስልጠናው ዋና ዓላማ  የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለት በመከላከል የህብረተሰቡ ጤና ለመጠበቅ የበጎ ፈቃደኞችን ሚና በማሳደግ የደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል።

የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በማድረግ የወንዝና ወንዝ ዳርቻ ስለማልማትና ከብክለት ስለመከላከል፣ ስለተከለከሉ ተግባራትና ቁጥጥር፣ ስለ ተቆጣጣሪው ተግባርና ኃላፊነት፣ ጥቆማና አቤቱታ አቀራረብ፣ ስለ አስተዳደራዊ እርምጃ አወሳሰድ እና ተደጋጋሚ ቅጣትና መሰል ጉዳዮች የዳሰሰ ሰነድ በባለስልጠኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ በሆኑት አቶ ናታናን ታዬ ቀርቧል።

በቀረበው ሰነድ በመቀጠል የበጎ ፈቃደኞችን ግንዛቤ ከማስጨበጥ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች ምን ይመስላሉ ፣ በጎ ፈቃደኞች ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በቅንጅት የመስራት ሂደቱና ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ያለበት ደረጃ እና እየገጠሙ ባሉ የግንዛቤ ክፍተቶች ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በማንሳት ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎች ባነሷቸው የግልጸኝነት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ከመድረክ ምላሽ በመስጠት በቀጣይ እንደክፍተት በተጠቀሱ የግንዛቤና የደንብ መተላለፎች ዙሪያ ከተቋሙ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ በመግለጽ ስልጠናው ተጠናቋል።

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments