ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስናን መከላከል ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስናን መከላከል ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

25/03/2018 ዓ.ም
ሰንዳፋ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለሁለተኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ የአቅም ግንባታ ሰልጣኝ አመራርና ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና በመከላከል ዙሪያ  ሰንዳፋ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ ግምገማዊ ስልጠና ሰጥቷል

በስልጠናው የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና የቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደ መስቀል ተቋሙን ከስነ-ምግባር አኳያ በጥንካሬ እና በድክመት የሚታዩና ነባራዊ ሁኔታ ፣ የደንብ መተላለፍ መንስኤና ተፅዕኖ ፣ ተግዳሮትና የመፍትሄ ኃሳቦች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦች በጥልቀት የያዘ ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ግምገማዊ ስልጠና ተሰጥቷል

ከቀረበው ሰነድ በመነሳት ፈጻሚዎች ከቅርብ ኃላፊ ጋር ስላለው መልካም ግንኙነት፣ 24/7 ስምሪት አሰጣጥ ላይ በሚፈጠሩ የመናበብ ክፍተት፣ ደንብ በማስከበር ሂደቱ ላይ መወሰድ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ስለሚገጥሙ ተግዳሮቶች፣ ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ እና በስነምግባር የታነፀ ኦፊሰር ከመፍጠር አንጻር መወሰድ ስለሚገባቸው የመፍትሄ ሀሳቦች ከሰልጣኞች በማንሳት ሰፊ ውይይት ተካሂድዋል

በመጨረሻም በተነሱ ጥያቄና ሀሳቦች ላይ በባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እና የስልጠና አስተባባሪዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ ተቋሙ ለሚደረገው ትውልድን በስነ-ምግባር የመገንባትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ጉዞ ከስልጠናው በወሰዱት እውቀት በመታገዝ የተሻሉ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ የጋራ በማድረግ ግምገማዊ ስልጠናው ተጠናቋል

ዘገባው የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments