የፈጠራ ባህል መፍጠር (creating a culture of creativity) እና ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
የፈጠራ ባህል መፍጠር (creating a culture of creativity) እና ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ህዳር 23/2018
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለማዕከል ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች ፣ ለክፍለ ከተማ ቡድን አስተባባሪዎች እና የስልጠና ባለሙያዎች የፈጠራ ባህል መፍጠር (creating a culture of creativity) እና ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለስልጣኑ የግንዛቤ ፈጠራ ላይ ትኩረት በመስጠት በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑንና በዚህም የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩን በተለያዩ ዙሮች ማሰልጠኛ በማስገባት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል ።
የዛሬው ስልጠናም የፈጠራ ባህልን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻልና ተቋማዊ ተግባቦት እንዴት መፍጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ስለሆነ የሚሰጡትን ስልጠናዎች በትኩረት በመከታተል እንደሚገባ አሳስብዋል ።
የፈጠራ ባህል መፍጠር (creating a culture of creativity) እና በተግባቦት ክህሎት ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ አመራር አካዳሚ ከፍተኛ አሰልጣኝ አቶ ወልደመድህን መኮንን ተሰጥቷል።
ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት ዙርያ ስልጠና የሰጡት የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የከተማ አመራር ልማት ዳይሬክተር እና ከፍተኛ አሰልጣኝ የሆኑት ወ/ሮ ነፃነት የምሩ ሲሆኑ ተግባቦት ለአንድ ተቋም ስኬትና ውጤት አንዱ መለኪያ እነደሆነ፣ የመሪና የተመሪ ተግባቦት ለስራ ቅልጥፍና እንደሚጠቅም ፣ ለአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ጉልህ ሚና እንዳለው እና በተቋም ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ጤናማ ተግባቦት እንደሚኖራቸው በስልጠናው ተመላክቷል ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments