የባለስልጣኑ የ2ኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የ2ኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሂደት የመስክ ምልከታ ተደረገ

የባለስልጣኑ የ2ኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሂደት የመስክ ምልከታ ተደረገ

              22/03/2018 ዓ.ም
          ** አዲስ አበባ **

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ሰንዳፋ ካምፓስ ለአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር  ባለስልጣን ኦፊሰሮች እየተሰጠ ያለው የአካል ብቃትና የንድፈሀሳብ ስልጠና የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣ በስልጠናው አስተባባሪዎች እና በዩንቨርስቲው አመራሮች የስልጠና ሂደቱን ምልከታና ጎብኝት ተደርጓል።

በመስክ ምልከታው ስልጠናው በተያዘለት ጊዜና ፕሮግራም  በጥሩ ዲሲፕሊን  እየተሰጠ መሆኑን ተመልክተዋል።

ሰልጣኞቹ የተግባቦት ጥበብ በንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሀገር ወዳድነት፣የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣የሃይል አጠቃቀም፣ አገልግሎት አሰጣጥ እና የአካል ብቃት ስልጠና በተገቢው መንገድ እተከታተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በበኩላቸው እየተሰጣቸው ያለው ስልጠና ለቀጣይ ስራቸው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው ስልጠናው በቀጣይ ቀናትም በተዘጋጀው ፕሮግራም መሰረት እንደሚቀጥል ተገልጿል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments