ባለስልጣኑ "የመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ "የመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ"በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ አካሄደ

ባለስልጣኑ "የመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ"በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ አካሄደ

            20/03/2018 ዓ.ም
            **አዲስ አበባ**     

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ "በሚል መሪ ሀሳብ በ2018 በጀት ዓመት የሚከናወኑ የአጭር ጊዜ እቅድ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሀገራችንን እንዲሁም ከተማችን እያሳዩ የሚገኘውን ፈጣን እድገት ለማስቀጠልና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት በስልጠናው በጨበጥነው ሞራል በከፍተኛ ተነሳሽነትና በላቀ ቁርጠኝነት ወደ ስራ መግባት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል ።

አክለውም የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን በማስፋት የግንዛቤ ስራዎች በማጠናከርና በማስፋት የቁጥጥርና የእርምጃ አወሳሰድ ተግባራትን መቀነስ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ የ2018 በጀት ዓመት የአጭር ጊዜ እቅድ በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ አቅርበዋል ።

በከተማችን የደንብ መተላለፍ በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም የስልጠና ግንዛቤ ስራዎችን በማጠናከር የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊና ተደራሽ በማድረግ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እና ባለቤት በማድረግ ህገወጥነት በከተማችን እንዲቀንስ ማስቻል እንደሚገባ በሰነዱ ተገልጿል ።

የሌብነትና ብልሹ አሰራር በመታገል የ 7/24 የስራ ባህልን በማዳበር በበጀት ዓመቱ ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የቀጣይ ሰራዎች ላይ በእቅድ መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን የባለሥልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።

በማጠቃለያው አመራሩና ሰራተኛው  በስነ-ምግባር የታነፀ ከብልሹ አሰራር የጸዳ  የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የሚሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መፈጸም የሚችል ለሌሎች አካላትና በስሩ ለሚገኙ ሰራተኞች አርአያ በመሆን ሌት ተቀን መትጋት እንደሚገባ ዋና ስራ አስኪያጁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments