ባለስልጣኑ በወቅታዊ የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ከክፍለ ከተማ ተወካዮችና እና ከወረዳ አመራሮች ጋር የስራ ግምገማ አካሄደ
ባለስልጣኑ በወቅታዊ የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ከክፍለ ከተማ ተወካዮችና እና ከወረዳ አመራሮች ጋር የስራ ግምገማ አካሄደ
ህዳር 17/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አደራሽ የግምገማ መድረክ ተካሄደ ።
ግምገማውን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህን ስራዎች ስንሰራ አመራሩ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩን በሚገባ ማወቅ እንዳለበት በተለይም ማህበረሰቡ ስለ ደንብ ማስከበር ያለውን ያለውን ግንዛቤ ጠንቅቆ ማወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።
አያይዘውም በደንብ ጥስቶች ዙርያ እርማጃ ከመውሰድ ይልቅ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ለማህበረሰቡ በመድረክ በቤት ለቤት የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መሰራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
ዋና ስራ አስኪያጁ የሽፍት አስተባባሪዎች እና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ በአፈር አዳይቱ እና በሰንዳፋ ማስልጠኛ ማዕከሎች በስነምግባር ፣ በአቋምና በእውቀት ላይ ተመስርተው ስራዎችን እንዲሰሩ ስልጠናዎች እየተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮቹ በደንብ ጥሰቶች ዙርያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ሲሰሩ ለማህበረሰቡ የሚያስከትለውን ጉዳት በማሳወቅና ደንቡን በማስረዳት በቀናነት ማገልገል እንደሚገባ እና በማህበራዊ ሚድያዎች የባለስልጣኑን ገፅታ መገንባት እንደሚገባ የመሳሰሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
በመጨረሻም በባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገበው ፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments