ባለስልጣኑ በመጀመሪያ ዙር የአካል ብቃትና የስነ-ምግባር ስልጠና ለወሰዱ አመራር እና ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የስራ ስምሪት ሰጠ
ባለስልጣኑ በመጀመሪያ ዙር የአካል ብቃትና የስነ-ምግባር ስልጠና ለወሰዱ አመራር እና ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የስራ ስምሪት ሰጠ
17/03/2018 ዓ.ም
** ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለአመራሩ እና ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በመጀመሪያ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የአካል ብቃትና የስነ-ምግባር ስልጠና የማጠቃለያ ፕሮግራም የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በተገኙበት ተካሂዷል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከተማችን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ መዲና ፣ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መቀመጫ እንዲሁም የቱሪስት መስብ በመሆኗ ውብና ጽዱ እንድትሆን የመጠበቅና የማስቀጠል ሰፊ ተልዕኮ የተሰጠን እንደመሆኑ በርካታ ተግባራቶች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን ይህንኑ ተግባር ለማስቀጠል አቅማችንን ከወቅቱ ጋር እየገነባን መሄዱ አስፈላጊ ስለሆነ የባለስልጣኑ አመራርና ኦፊሰሮችን በማሰልጠን በከተማው አስተዳደር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት ለመፈጸም የሚያስችል ተግባራትን ለማከናወን የተሰጠው ስልጠና ሰፊ ጥቅም እንደሚኖረው ገልጸዋል ።
ስልጠናው ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች መሰጠቱን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው ተመራቂዎቹ ወደ ስራ ቦታቸው ሲሔዱ በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን በሚገባ በማስተካከል ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ፍጹም ዲሲፕሊን በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በማጠቃለያው ስልጠና ለወሰዱ አመራር እና ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የቀጣይ የስራ ስምሪት ተሰጥቷል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments