በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ የሚሰጠው ስልጠና...

image description
- In code inforcement    0

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ የሚሰጠው ስልጠና የተግባቦት ክህሎት በማሳደግ በሙያዊ ስነ-ምግባር አገልግሎት ለመስጠት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ የሚሰጠው ስልጠና  የተግባቦት ክህሎት በማሳደግ በሙያዊ ስነ-ምግባር አገልግሎት ለመስጠት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገለፀ።

11/03/2018 ዓ.ም
ሰንዳፋ

ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ የሚሰጠው ስልጠና በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  ስራዎችን በእውቀትና በቴክኖሎጂ በተደገፈና በሙያዊ ስነ-ምግባር አገልግሎት ለመስጠት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገለፀ ።

በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርስቲ እየተሰጠ ያለው የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችና አመራሮች  ስልጠና እስካሁን በንደፈ ሀሳብ ዙርያ  በሀገር ወዳድነት ፣ በተግባቦት ክህሎት ፣ በሰብዓዊ መብት ፣ በህገ መንግስት ፣ በሀይል አጠቃቀም ፣ በቴክኖሎጅ  አጠቃቀም እና የተለያዩ ወታደራዊ ስልጠናዎችን ጨምሮ መስጠቱ  ተገልጿል

በስልጠናውም ኦፊሰሩና አመራሩ በአሰራር ላይ የሚገጥማቸውን ክፍተቶች በመሙለት በቂ ቁመናና የቴክኖሎጅ አጠቃቃምን ለማሳደግ ሀገርን በመውደድ በተግባቦትና ህግና ደንቦችን በማወቅ ህዝብን ማገልገል የሚያስችል ስልጠና በመሰጠት ለይ እንደሚገኝ ስልጠና በማስተባበርና በመሰልጠን ላይ የሚገኘኙት የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር አቶ ደሳለኝ ለጋስ ገልጸዋል

ስልጠናው  በሰነምግባረ በመታነፅ ለመስክ ስራ በሚጠቅም መልኩ በወታደራዊ ስልጠናዎች በመሰጠት ላይ እንደሚገኝና ከስልጠናው ማህበረሰቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚቻል የሚያግዝ መሆኑ በመግለፅ ሁሉም የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር እና አመራር ስልጠናውን በትኩረት በመውሰድ ክህሎታቸው  ለማሳደግ ሰልጣኞች ገልጸዋል።

የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችና አመራሮች የንድፈ ሀሳብ እና ወታደራዊ ስልጠናዎች በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ  የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments