ባለስልጣኑ ባለፉት አራት ወራት በሚዲያ አየር ሰ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ባለፉት አራት ወራት በሚዲያ አየር ሰዓት በመጠቀም ያከናወናቸውን ስራዎች ገመገመ።

ባለስልጣኑ ባለፉት አራት ወራት በሚዲያ አየር ሰዓት በመጠቀም ያከናወናቸውን ስራዎች ገመገመ።

               11/03/2018 ዓ.ም
                **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት አራት ወራት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የቴሌቪዝንና ሬዲዮ አየር ሰዓት በመጠቀም ያከናወናቸውን የተለያዩ ፕሮግራሞች የሁለቱም ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በባለስልጣኑ ሚኒ አዳራሽ ገምግሟል።

በግምገማውም ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2:00 ሰዓት ዜና በኃላ ለ30 ደቂቃ በቴሌቪዥን እና ዘወትር እሮብ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ለ30 ደቃቂ በኤፍ.ኤም ሬዲዮ 96.3 ላይ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በመተባበር  የተከናወኑ እና አየር ላይ የዋሉ ስራዎችን ሪፓርት በባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የሬድዮ፣ ቴሌቪዥንና ህትመት ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ሔኖክ ታደሰ የቀረበ ሲሆን በሪፓርቱም የተሰሩ ስራዎች፣ የታዩ ክፍተቶችና ውጤቶች  ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲሁም የቀጣይ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የቴሌቪዥን ዘርፍ ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ታደሰ በመድረኩ የተገኙ ሲሆን ሚዲያው ከተቋሙ ጋር በጋራ በመሆን ባከናወናቸው ስራዎች የባለስልጣኑን የግንዛቤ አድማስ ማስፋት የተቻለ መሆን ጠቅሰው፤ በቀጣይ የአቀራረብ ይዘቱን በማሻሻል ይበልጥ ሳቢ በማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር እየተሰሩ  የሚገኙት ፕሮግራሞች ከተቋም ገጽታ ግንባታ፣ ደንብ መተላለፎችን ከመከላከል እና ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር መልካም ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክና የኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬቱን አመስግነዋል ።

በውይይቱ በቀጣይ በሚሰሩ ፕሮግራሞች ላይ የይዘትና የአቀራረብ ማሻሻያዎችን በማድረግ ይበልጥ ህብረተሰቡ ጋር በመድረስ ተቋሙ በ2022 የወጠነውን ራዕይ ለማሳካት በይበልጥ ሚዲያዎችና ልዩ ልዩ የሚዲያ ፕላትፎርሞች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments