የባለስልጣኑ የአካል ብቃትና የንድፈሀሳብ ስልጠና...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የአካል ብቃትና የንድፈሀሳብ ስልጠና በተያዘለት ጊዜና በጥሩ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ

የባለስልጣኑ የአካል ብቃትና የንድፈሀሳብ ስልጠና በተያዘለት ጊዜና በጥሩ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ

           09/03/2018 ዓ.ም
          ** አዲስ አበባ **

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ለአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር  ባለስልጣን ኦፊሰሮች እየተሰጠ ያለው የአካል ብቃትና የንድፈሀሳብ ስልጠና የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እና የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ የስልጠና ሂደቱን ጎብኝተዋል።

በተመለከተ ባደረጉት የመስክ ምልከታ ስልጠናው በተያዘለት ጊዜናፕሮግራም  በጥሩ ዲሲፕሊን  እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልጣኞቹ  በዛሬው እለት የተግባቦት ጥበብ የንድፈ ሀሳብ እና የአካል ብቃት ስልጠና በተገቢው መንገድ እተከታተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በበኩላቸው እየተሰጣቸው ያለው ስልጠና ለቀጣይ ስራቸው እጅግ ጠቃሚ እንደሆነና በጥሩ ሁኔታ እየተሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ስልጠናው በቀጣይ ቀናትም በተዘጋጀው ፕሮግራም መሰረት እንደሚቀጥል ተነግሯል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments