ባለስልጣኑ በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞቹን ፎቶ በማ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞቹን ፎቶ በማንሳት ያልተረጋገጡ መረጃዎችን የሚያጋሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠብ አሳሰበ

ባለስልጣኑ በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞቹን  ፎቶ በማንሳት ያልተረጋገጡ መረጃዎችን የሚያጋሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠብ አሳሰበ

             08/03/2018 ዓ.ም
           **አዲስ አበባ**     

ባለስልጣኑ ሰሞኑን በማህበበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ  2  ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ህዳር 5 2017 ዓ.ም ኦፊሰሮች ከደምበል ወደ ቦሌ በሚወሰድው በኮሪደር ልማት በለማ የመናፈሻ ሳር ላይ በመኪና በመሄድና ጉዳት ያደረሰችው አሽከርካሪ በደንብ ቀጥር 167/2016 የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ተራ ቁጥር 20.2 መሰረት አምስት ሺ ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰዱ ይታወቃል።

ጉዳት ያደረሰችው አሽከርካሪ በጊዜው ልጅ ታሞብኛል በማለት እዛው አከባቢ እንደምትሰራ ለጥፋቱም የሚቀጡትን ቅጣት ለመክፈል ፈቃደኛ በመሆን ሰራተኛቸውን እንደሚልኩ በቦታው ተመድበው ለሚሰሩ የደንብ ማስከር ኦፊሰሮች እየገለፁ በነበረበት ወቅት ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ቪድዮ በመቅረጽ የተቋሙን ገጽታ ለማጥፋትና የደንብ ማስከበር ስራው ለማስተጓጎል የተለቀቀው መረጃ አግባብነት የሌላለው መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2017 አንድ ሹፌር በደንቡ የተገለፁ ጥፋቶችን ሲፈፅም በደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ተገቢውን ቅጣት ሊቀጣ እንደሚችል ስልጣን የተሰጠው መሆኑና ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ግንዛቤ መፍጠሩ ገልጿል።

ተቋሙ ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ  በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ መገልገልና መጠቀም እንዳለበት አሳስቧል ፡፡

ባለስልጣኑ ከዚህ በፊት በኮልፌ፣በየካ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞቹን ያለ-ፈቃድ ፎቶ በማንሳት ሶሻል ሚዲያ በማጋራት በወንጀል ተጠያቂ ያደረገ መሆኑን በመግለፅ ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀሙ ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመነጋገር መረጃ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።

በከተማዋ ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ የተቋሙን ስም የሚያጠለሽ ያልተረጋገጠ መረጃዎችን በማጋራት ህብረተሰቡን የሚያሳስቱ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ባለስልጣኑ  አስታውቋል ።

የከተማው ነዋሪ በሚኖርበት አካባቢ ህገወጥ ተግባራትን  ካስተዋሉ እና ማንኛውም ጥያቄ ሲኖረው በነፃ ስልክ 9995 ጥያቄ እንዲያቀርብ እና መረጃ እንዲሰሰጥ ጥሪውን አስተላልፎዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments