የአገልጋይና የተገልጋይ ግንኙነት ለማጠናከር የመማክርት ጉባዔ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
የአገልጋይና የተገልጋይ ግንኙነት ለማጠናከር የመማክርት ጉባዔ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
4/3/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከ11 ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ የመማክርት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚዎችና ለሲቪል ማሀበራት ስራ አስፈፃሚዎች በመማክርቱ አጠቃላይ አሰራር ዙርያ እና በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ማንዋል ላይ ስልጠና ተሰጠ።
የስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ባለስልጣኑ ከተማዋን ንፁህ ፣ ፅዱና ከማንኛውም የደንብ ጥሰቶች የፀዳች ከተማ ለማድረግ በርካታ ሀላፊነት ተሰጥተውት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የጽ/ቤት ኃላፊው አክለው ባለስልጣኑ የሚከላከላቸውን የሚቆጣጠራቸውን እና እርምጃ የሚወሰድባቸውን የደንብ መተላለፎች በመጥቀስ የመማክርት ጉባኤው ከተለያዩ አደረጃጀቶች የተውጣጡ በመሆናቸው የባለስልጣኑ ተገልጋዮች ከባለስልጣኑ ጋር ለማገናኘት ወሳኝ በመሆናቸው ስልጠናውም እንዴት መስራት እንዳለብን የሚግዝ መሆኑን ገልጸዋል ።
ስለጠናውም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ፍቅሬ ተሰጥቷል።
ስልጠናው በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ማንዋል ዙርያ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፈ ለማድረግ ከመንግስት በተጨማሪ የተገልጋይ፣የባለድርሻ አካላት ፣የሲቪክ ማህበራት፣ የሚዲያዎች አና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
የመማከረት ጉባኤው እቅድ ፣ ብዝሀነት/አካታች መሆን/ ፣ በጋራ መስራት፣ ለመማር ዝግጁ መኖር ፣ ግልፅነትና መተማመን እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት የመሳሰሉትን መርሆች ይዘው መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።
በመጨረሻም ስለጠናው ለመመካረት ጉባኤው አሰራር ጠቃሚ እንደነበረ እና አገልግሎቶች በተገቢው ሁኔታ እንዲካሄዱ የሚያደረግ በተገልጋይና በአገልግይ መካከል ሰላማዊ ትስስር እንደሚፈጥር ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
መረጃው፦ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments