የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት...

image description
- In code inforcement    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ በደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ በደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሄደ

               02/03/2018 ዓ.ም
              **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመገኘት በወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም ፣የተከናወኑ ተግባራትና ቅንጅታዊ አሰራር  ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሂዷል::

የከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ኦልያድ ቡልታ በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙሪያ ለህብረተሰቡ የተደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች መከናወኑን ማየት መቻሉን ገልፀው በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

አክለውም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ወደ ህብረተሰቡ በአግባቡ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች በቂ ግንዛቤ እያገኙ መሆኑ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ የመጣው ቡድን ተቋሙ በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙሪያ ያከናወናቸውን ስራዎች እንዲሁም ለግንዛቤ የተዘጋጁ ሰነዶቹንና ግንዛቤ የተፈጠረላቸውን አካላት የሚያሳዩ ሰነዶቹን ምልከታ አድርገዋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments