አለርት ሆስፒታል በካይ ኬሚካል ወደ ወንዝ በመልቀቁ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን/ ብር መቀጣቱ ተገለፀ
አለርት ሆስፒታል በካይ ኬሚካል ወደ ወንዝ በመልቀቁ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን/ ብር መቀጣቱ ተገለፀ
26/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ጋራ በመሆን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቀው አለርት ሆስፒታል የመንግስት ተቋም ላይ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን/ ብር በመቅጣቱ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
የተካሄደው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታ ዘነበ ወርቅ አለርት ሆስፒታል ብክለቱ በከተማው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች በላብራቶሪ የተረጋገጠ በመሆኑ በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 1,000,000 (አንድ ሚልየን )ብር የተቀጣ መሆኑ ተገልጿል።
በክፍለ ከተማው በወረዳ 4 በወንዝ ዳርቻ ብክለት የፈፀሙ 6 ላቢያጆዎች እያንዳንዳቸው 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር በድምሩ 600,000/ስድስት መቶ ሺህ/ ብር በመቀጣት በክፍለ ከተማው በእለቱ በአጠቃላይ 1,600,0000/አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ተገልጿል ።
ባለስልጣኑ በተደጋጋሚ በተለያዩ አማራጮች የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እየሰራ ቢሆንም ከህገ ወጥ ተግባራቶች በማይታቀቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ ነዋሪዎችና ተቋማት ከመሰል ተግባራቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል።
የከተማው ነዋሪ በሚኖርበት አካባቢ ህገወጥ ተግባራትን ሲከናወኑ ካስተዋሉ በነፃ ስልክ 9995 ጥቆማ እንዲሰሰጥ ተቋሙ ጥሪውን አስተላልፎዋል።
መረጃው፦የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments