ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት የውል ስምምነት አካሄደ ።
ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት የውል ስምምነት አካሄደ ።
25/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለአመራሮችና ለኦፊሰሮች የአጭር ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር የባለስልጣኑ እና የዩኒቨርስቲው አመራሮች በተገኙበት የውል ስምምነት ፊርማ አካሄደ ።
በስምምነቱ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ አመራሩና ኦፊሰሩ አቅም ለማሳደግ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ዩንቨርስቲው ወቅቱን የጠበቀ ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ በበኩላቸው ተቋሙ እና ከተማው የሰጣቸው ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል ስልጠና ልምድና እውቀቱ ባላቸው አሰልጣኞች እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments