ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን) ብር መቅጣቱን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን) ብር መቅጣቱን አስታውቋል።
23/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች በወንዞችና ወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን) ብር መቅጣቱን አስታውቋል።
ቅጣቶቹ በቂርቆስ ክ/ከተማ በወረዳ 05 ኖክ ማደያ ቡልጋርያ ያልተጣራ ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 400,000 ብር በወረዳው የቡልጋሪያ ሳይት ማሳያና ማምረቻ ማህበር የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 300,000 ተቀጥተዋል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መሰረት ዘውዱ እና ጓደኞቻቸው ላብያጆ የመኪና ዘይትና ነዳጅ ፍሳሽ ቀጥታ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 400,000ብር ፤ብሩክስ ህንፃ የህንፃው ሽንት ቤት ፍሳሽ ቀጥታ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 300,000ብር ተቀጥቷል።
በተመሳሳይበየካ ክ/ከተማ ግሬት ሲቲ ሞል መጥፎ ሽታ ያለው ፍሳሽ ወደ አስባልት በመልቀቅ 300,000 ሺህ ብር ሲቀጡ በአቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ካፍደም ኘላዛ ትሬድንግ 300,000 ብር ቅጣት የተሠጣቸው ሲሆን በተደጋጋሚ ግንዛቤ ተሠጥቷቸው ማረም ያልቻሉ ናቸው።
በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments