ባለስልጣኑ የዲጅታል የመስክ ስራ አስተዳደር ላይ ለማዕከል ዳይሬክተሮች ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ የዲጅታል የመስክ ስራ አስተዳደር ላይ ለማዕከል ዳይሬክተሮች ስልጠና ሰጠ
22/02 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለማዕከሉ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈአገልግሎት ለማስጀመር የመስክ አስተዳደር /Field managmet system/ ስልጠና ተሰጥቷል ።
ባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በቀጣይ ወራት አገልግሎቶቹን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እና ተቋሙ በማዘመን ከወረቀተ ንክኪ ነጻ ፣ ቀልጣፋና ውጤት ተኮር ተግባራትን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መረጃዎች በማስደገፍ እንደሚከናወን ገልጸዋል ።
አክለውም ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል የመረጃ ሥርዓት አያያዝ ስርዓትና የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት ስርጋታ ስራ መጀመሩ ገልፀዋል።
ስልጠናው አገልግሎቱ ለማስጀመር ሰራተኛውና አመራሩ የአሰራር ፣የእውቀት እና የክህሎት ክፍተት እንዳይፈጠር ታሳቢ መደረጉን ገልፀው በቀጣይም ለክፍለ ከተማና ለወረዳ አመራሮች እና የሚመለከታቸው ለባለሙያዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል ።
ተቋሙን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀት የኔትወርክ መሰረት ልማት ስራዎችን ዘርግቶ በማጠናቀቅ በራስ አቅም የተሰሩ ሶፍትዌሮችን ወደ ተግበር ለማስገባት የሚያግዝ ስልጠና መሆኑን የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ካሳሁን ተናግረዋል ።
የመስክ አስተዳደር /Field managmet/ ስልጠና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በመጡ የሶፍትዌር ኢንጅነር ባለሙያ አቶ አማኑኤል መኮንን እና የሶፍትዌር ፕሮግራመር ባለሙያ አቶ ሀብታሙ ፔጥሮስ ተሰጥቷል ።
ተቋሙ የሚያከናውነውን ተግባራት በአንድ ሲስተመ ውስጥ በማካተት ወጥ የሆነ መረጃ አያያዝ ስርዓትን በመዘርጋት ከወረቀት ንክኪ የጸዳ ምቹ እና ቀልጣፋ ስራ ለማከናወን የበለጸገው ስፍትዌር የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments