ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት የፓለቲካ ባህላችንን የዳበረ ሊሆን ይገባል" ዶ/ር ተስፍዬ ጅማ የአዲስ አበበ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር
"ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት የፓለቲካ ባህላችንን የዳበረ ሊሆን ይገባል" ዶ/ር ተስፍዬ ጅማ የአዲስ አበበ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር
20/02/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር አብይ አሕመድ 4ተኛ መፅሀፍ በሆነው የመደመር መንግስት መፅሀፍ ዙሪያ ከተቋሙ መላው ሰራተኛ ጋር ከአዲስ አበባ እና ከፐፕሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በመጡ ምሁራን አማካኝነት በዛሬው ዕለት የፓናል ውይይት ተካሂዶል።
የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ከፍያለው ታደሰ የተቋማችን እቅድ ግቡን እንድናሳካ የሚረዳን በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮችን የያዘና ሰፊ እውቀትን የምናገኝበት የፓናል ውይይት በመሆኑ በትኩረት መከታተል እንደሚገባ ገልጸዋል።
የፓናሉ አወያይ የሆኑት ዶ/ር ተስፍዬ ጅማ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት የፓለቲካ ባህላችንን የዳበረ ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጡት ዶ/ር ሙሉጌታ አየለ በአጠቃላይ መፅሀፉን ያዮበትን ሁኔታ ሲገልፁ ኢትዪጵያ ትናንት፣ዛሬና ነገ ምን ትመስላለች በሚሉት ሀሳቦች ላይ ሰፊ ትንታኔ አቅርበው የሀገሪቷ እጣፈንታ በዜጎቿ እጅ ላይ መሆኑንምና የመፍትሄውን መንገድ በመፅሀፉ ላይ በግልጽ መቀመጡን አመላክተዋል።
ሌላኛው በመፅሀፍ ላይ ትንተና የሰጡት ዶ/ር ታምሩ ፈይሳ መጽሐፉ 13 ምዕራፍ እና 3 ክፍል የያዘ ሲሆን የእርስ በእርስ መተማመንና ሀገራዊ የብልፅግና መንገዶችን በራስ ርዕዮተ ዓለም ያሳየ መሆኑን አብራርተዋል።
የተቋሙ የፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፍሁን አሉላ የፓናል ውይይቱ የተዘጋጀበት አላማ ለሀገራችን እና ለከተማችን እድገት የተቋማችንና የራሳችን ሚና ለማመላከት መሆኑ ገልፀው የመደመር መንግስት መፅሀፍ ከዚህ ቀደም በጠቅላይ ሚኒስትራችን ከተፃፍትን ሀገርን የሚያሻግር ሀሳቦችን በጥልቀት የሚተነትን እና ሁሉም ዜጋ የራሱን ሚና መወጣት እንዳለበት የሚያመላክት መሆኑን አመላክተዋል።
የተቋሙ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው የፓናል ውይይቱ መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት ሙህራኖች አመስግነው ይበልጥ መፅሀፎችን ለማንበብ ያነሳሳል ሲሉ ተናግረው ሀገራችን ወደ ብልፅግና ማማ ለመጓዝ መደመር አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን ገልፀዋል።
በውይይቱ በተጋባዥ እንግዶች በቀረበው የመነሻ ሀሳቦች መሰረት በማድረግ እና በመፅሀፍ መሰረታዊ ሀሳቦች ላይ ከሰራተኞች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments