ባለስልጣኑ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ለማከናውን የሲስተም ዝርጋታ የደረሰበት ደረጃ ተገመገመ
ባለስልጣኑ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ለማከናውን የሲስተም ዝርጋታ የደረሰበት ደረጃ ተገመገመ
18/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አገልግሎትና ተግባራቶቹን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የሚያስችል አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ለማከናውን የሲስተም ዝርጋታ የደረሰበት ደረጃ የባለስልጣኑ አመራሮች እና የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ከሶፍትዌር እና ከፕሮጀክት ዝርጋታ ሰራተኞች በተገኙበት ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ለተገልጋይ እና ለአገልጋይ ወጪና ጊዜ ቆጣቢ ቴክኖሎጂ በመፍጠር ተቋሙን ከዘመኑ ጋር ለማራመድ የቴክኖሎጂ ስራዎች መጀመር እንዳለባቸው ገልፀዋል::
አክለውም ተቋሙ የእቅዱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ግልፅ አሰራር ለመዘርጋት፣ ከወረቀት ነፃ አገልግሎት ለመስጠት፣ የመረጃ አያያዝ በማዘመን ደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን በአንድ ማዕከል ለመቆጣጠር እንዲሁም ብልሹ አሰራርን በመቀነሰ የተገልጋይን እርካታ ለመጨመር የሚረዳ አሰራር ስርአት ቴክኖሎጂ ለመዘርጋት ስራዎች መጀመራቸው ጠቁመዋል::
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በባለስልጣኑ ፊልድ ማኔጅመንት፣ስማርት ኦፊስ፣ሲቲዝን ኢንጌጅመንት፣የእቅድ አመራር እና ምዘና ማኔጅመንት እና የጥሪ ማዕከል ሲስተም ለመዘርጋት እና ስራዎች ለማስጀመር መዘጋጀቱን ገልፀዋል::
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ መረጃዎች:-
https://linktr.ee/aacodeenforcement?utm_source=linktree_admin_share
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments