ባለስልጣኑ በጥናት አዘገጃጀት ዙርያ ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ በጥናት አዘገጃጀት ዙርያ ስልጠና ሰጠ
ጥቅምት 5/2018
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጥናት አዘገጃጀት ዙርያ ለማዕከሉ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች እና የክፍለ ከተማ የስልጠና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የባለስልጣኑ የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት በተለያዩ የደንብ መተላለፎች ዙርያ ጥናቶች መስራቱን ጠቁመው በ9ኙ የደንብ መተላለፎች ዙርያ ምንጮች ለማወቅ እና ችግር ፈች ጥናት ወሳኝ በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ችግሮችን በመለየት ወደ መፍትሄ መግባት እንደሚችል አስገንዝበዋል።
ስልጠናው ከአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ተፈራ ሙሉነህ ተሰጥቷል።
በስልጠናው ጥናት እንዴት እንደሚዘጋጅ፣ ስለ ጥናት አይነቶች ፣ ሰለ አጠናን ዘዴዎች፣ ጥናት ችግርን ለመፍታትና የችግሩን ዋና ምንጭ ለማወቅ እንደሚረዳ፣ ሰለ ጥናት አዘገጃጀት ቅደም ተከተል ዳራ ፣አለማ፣ወሰን ፣የተዛማጅ ጥናት ቅኝት እና ስለ ጥናት መሰረታዊ ባህሪ በመሳሰሉት ዙርያ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ጥናቶች በማዕከል ደረጃ ብቻ ሳይሆን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ መጠናትና ስላለባቸው ሰልጣኞች የወሰዱት ስልጠና እስከታች እንዲወርዱ እና ጥናቶች እንዲሰሩ አቅጣጫ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል ።
ዘገባው ፦ የባለሥልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments