በአዋኪ ድርጊቶች እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል...

image description
- In code inforcement    0

በአዋኪ ድርጊቶች እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ዙሪያ የህዝብ ውይይት መድረክ ተካሄደ

በአዋኪ ድርጊቶች እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ዙሪያ የህዝብ ውይይት  መድረክ ተካሄደ

                  30/01/2018 ዓ.ም
                  ** አዲስ አበባ**
         
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኮልፌ ፣ በአራዳ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በአዋኪ ድርጊቶችን መከላከል ላይ፣ በደንብ ቁጥር 150/2015 እና በፀረ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ዙሪያ   በህዝብ ንቅናቄ መድረክ  በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ተፈጥሯል ::

በግንዛቤ መድረኮቹ አዋኪ ድርጊቶችን መከላከል እና በስነምግባር እና ብልሹ አሰራር መከላከል በሚል ርዕስ ለህብረተሰቡ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።

በመድረኩ ከአዋኪ ድርጊት ጋር በተያያዘ በተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ ተፈጥሯል በተለይም ደግሞ በት/ቤቶች ላይ ለተማሪዎች በቅ/መከላከል ባለሙያዎቻችን አማካኝነት በየጊዜው ግንዛቤ የመፍጠር ተግባር እየተከናወነ  እንደሚገኝ ተገልጿል ።

ህብረተሰቡ በአሁኑ ሰዓት  ህገ ወጥነትን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ስራ በማጠናከርና  ተባባሪ በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባና ከመሰል አዋኪ ተግባራት ልጆቻቸውና ራሳቸውን በማራቅ ለሌሎች አርዓያ መሆን እንደሚገባቸው በመድረኮቹ ተገልጿል ።

የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ደንቡና መመሪያውን ተፈፃሚ እንዲሆን እና በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ በማድረግ ለብልሹ አሰራር እና ፀረ ሙስና ተጋላጭነት መቆጣጠር መቻል ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል::  

በመድረኩ አዋኪ ድርጊትን በመከላከል ህብረተሰቡም ከደንብ ማስከበር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክረው መስራትና እርምጃ እንዲወሰድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው  ተነግሯል ።

ወጣቱን  ከአዋኪ  ድርጊቶችን እና ብልሹ አሰራሮችን  እንዴት እራሱን መከላከልና መቆጣጠር  እንደሚቻል በሰነዱ በዝርዝር ተገልፃል ።

በመጨረሻም ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በተሰጡ ሀሳብ አስተያየት ጥያቄዎች ላይ  ሰፊ ውይይት በማድረግ   ከመድረኩ  ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments