ባለስልጣኑ የመስከረም ወር መደበኛና ወቅታ ተግባራትን ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ገመገመ
ባለስልጣኑ የመስከረም ወር መደበኛና ወቅታ ተግባራትን ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ገመገመ
መስከረም 28/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመስከረም ወር በእቅድ አፈፀፀምና ወቅታዊ ስራዎች በተመለከ ከክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት አደረገ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የመስከረም ወር የአደባባይ በዓላት የነበሩበት ቢሆንም ከዚህ ጎን ለጎን በካስኬዲንግ የወረዱትን ተግባራት በጥራት መስራት መቻሉ ጠቁመዋል።
በውይይቱ የመስከረም ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ያቀረበ ሲሆን በወሩ የአደባባይ ሁነቶች ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ፣ በ9ኙ የደንብ ጥሰቶች የመከላከል ፣የመቆጣጠር እና አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰድ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።
በመድረኩ በድክመትና በጥንካሬ የታዩ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ እርምጃዎች በሪፖርቱ በዝርዝር ቀርበዋል።
በወሩ የተሰሩ ስራዎች ጠንካራ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች ላይ መረጃ በጥንቃቄ መሰራት እንዳለበት እና አስተዳደራዊ ቅጣቶች የቅጣት ደረሰኝ በትክክል መከፈላቸው መረጋገጥ እንደሚገባ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments