ባለስልጣኑ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀን የንግድ ተቋም 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱን አስታወቀ
ባለስልጣኑ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀን የንግድ ተቋም 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱን አስታወቀ
28/01/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እየተሰራ ባለው የአፍንጮ በር የወንዝ ዳርቻ ልማት በካይ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀን የንግድ ተቋም (ጠጅ ቤት) 3 መቶ ሺ ብር መቅጣቱን አስታውቋል።
የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ ዋና ሳጅን ውባለም ሽፈራው እንደገለፁት ድርጅቱ በተደጋጋሚ ወደ ወንዝ የሚለቀውን በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ እንዲያቆም ግንዛቤ ቢፈጠርለትም ከድርጊቱ መቆጠብ ባለመቻሉ ከክፍለ ከተማው የአካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት ጋር በመሆን የቅጣት እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ መሰል ደንብ መተላለፎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ገልፀው ደንብ ተላላፊዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል። እየሰሩም እንደሆነ ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ድርሻ በመሆኑ ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች 9995 ነፃ የስልክ መስመእንዲጠቀሙ ጥሪውን አቅርቧል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባልስልጣን ኮሙኒኬሽ ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments