ባለስልጣኑ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙ ከጠቅላላ ካውንስል ጋር ገመገመ

ባለስልጣኑ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙ ከጠቅላላ ካውንስል ጋር ገመገመ

                        27- 01 - 2018ዓ.ም
                     **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን ከባለሥልጣኑ ዳይሬክተሮች ጋር የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመክፈቻው እንዳሉት በዚህ ውይይት በሩብ ዓመቱ በተቋማችን የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶችን ለመፈተሽ ያስችለናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  የ2018 ዓ.ም በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ሰነድ በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል ።

በሰነዱ እንደተገለጸው  የተቋም የአቅም ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር፣የስራ አከባቢን ለሰራተኛውም ሆነ ለተገልጋይ  ምቹ ለማድረግ የሚዲያ ሽፍንን በመጠቀም የተቋም ገፅታ በመገንባትና ከተገልጋይ ጋር መድረክ በመፍጠር ግብዓት ለማግኘት መሠራቱን ገልፀዋል።

ኮነሬል አድማሱ ተክሌ ከሪፖርቱ እንደገለፁት በባለስልጣኑ በቦታ 6808 እንዲሁም በካሬ 11,798,292.38 የሚያህል መሬት እየተጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments