የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከ...

image description
- In code inforcement    0

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አዋኪ ተግባራት መከላከል እንዳለበት ተገለፀ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አዋኪ ተግባራት መከላከል እንዳለበት ተገለፀ

    27/ዐ1/2018 ዓ.ም
  አዲስ አበባ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና በስነምግባር ና ብልሹ አሰራር ዙሪያ  ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የተሰጠውን ተልዕኮ በመወጣት በዘጠኙም የደንብ መተላለፎች ላይ በመስራት  በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም ትውልድ ገዳይ የሆነውን አዋኪ ድርጊት በመከላከል ህብረተሰቡ ከደንብ ማስከበር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክረው መስራትና እርምጃ እንዲወሰድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው  ተናግረዋል ።
አክለውም ኃላፊዋ  ወጣቱን ትውልድ እያጠፍ ከአላማው እያስቀረ ያለውን አዋኪ ድርጊት  ተግባር በመቆጣጠር ምንም አይነት የደንብ መተላለፍ  እንዳይከሰት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው ለቀጣይም በዘጠኙም የደንብ መተላለፍ ተግባራት ላይ ሰፊ ስራዎችን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።

በመድረኩም አዋኪ ድርጊቶችን መከላከል በስነምግባር እና ብልሹ አሰራር መከላከል በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ቁምላቸው ቀርቧል አዋኪ ተግባራት በክፍለ ከተማው ምን እንደሚመስል ፣ አዋኪ ድርጊቶችን እንዴት መፍታት እና መከላከል እንደሚቻል በሰነዱ በዝርዝር ተገልፃል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱት ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት  መድረኩ ተጠናቋል ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments