ባለስልጣኑ “ከጂኦስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና” በሚል ርዕስ ውይይት አካሄደ።
ባለስልጣኑ “ከጂኦስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና” በሚል ርዕስ ውይይት አካሄደ።
27/01/2018ዓ.ም
*አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሀገራችን ስላለችበት እንዲሁም ከህዝቡ ምን ይጠበቃል፤ ያለንበት የጂኦ ስትራቴጂ ሁኔታ ምን ይመስላል በሚል በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ የተቋሙ አመራሮች እና መላው ሰራተኞች ውይይት አካሂደዋል።
ከጂኦስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና የሚለውን ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፍሁን አሉላ እንዳሉት ሀገራችን በተግዳሮቶች ውስጥ አልፋ ወሳኝ የሆነ ተጨባጭ ለውጥ አምጥታለች በዚህ ጊዜ አለም ከሉዓላዊነት ወደ አዲስ ጂኦስትራቴጂያዊ የበላይነት ላይ እየሄደች ነው ኢትዮጵያ ደግሞ በጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናቸው ከታደሉ ሀገሮች መካከል አንዷ መሆኖን ገልፀዋል።
አክለውም ከቁጭት ኩስመና ወጥተን እንበልፅግ ነገር ግን ይህን ለማድረግ የምናገለግለውን ህዝብ፣ የምንገነባውን ሀገር ፣የምናስከብረውን ብሔራዊ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ፅኑ አቋም መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
መድረኩን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት ሀገራችን ከታላላቅ ሀገራት መካከል የምትመደብ ነበረች የአክሱምን እና የላሊበላ አቢያተ ቤተክርስቲያንን እንደ ማሳያ ማየት እንደሚቻል እናወ ቀደመው ገናናነትዋ ለመመለስ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ይህንን ትልቅነታችንን ለመመለስ ኢትዮጲያዊ የሆነ ሰው በሙሉ የብሔር፣የሀይማኖት የባህል እንዲሁም የተለያዮ ልዮነቶች ቢኖረንም በሀገራችን ጉዳይ ግን አንድ ልንሆን ይገባል ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ሀሳብ አስተያየቶች ተሰተው ወይይት ተደርጎ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments