ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሆራ ፊንፊኔ የእሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ ለደንብ ማስከበር አመራሮችና ሰራተኞች ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት፦
ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሆራ ፊንፊኔ የእሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ ለደንብ ማስከበር አመራሮችና ሰራተኞች ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት፦
መስከረም 24/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ወጥቶ ያለምንም የፀጥታ ችግር ዕሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች፣ኦፊሰሮች እና ሰራተኞች ከፍተኛ ምስጋና አቀረቡ።
ዋና ስራ-አስኪያጁ እንደተናገሩት "ከበዓሉ አስቀድም በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቀን እና በሌሊት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ስምሪት በመውሰድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የባለስልጣኑ ማኔጅመንት አባላት፣የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮች፣ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ ዳይሬክተሮች እና የሲቪል ሰራተኞች ላደረጋችሁት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ እንደዚሁም የከተማው ነዋሪዎች በደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!"
በከተማው ከበዓሉ አስቀድሞ በዓሉ የሚከበርበት ቦታ በማስዋብ እና አካባቢውን በማፅዳት እንግዶቹን በየአካባቢው ባማረ መስተንግዶ በመቀበል፣ በዓሉ ሰላማዊ ድባቡን ይዞ እንዲጠናቀቅና የበዓል እሴቱንና ስርዓቱን ጠብቆ በከፍተኛ ድምቀትና በሰላማዊነት እንዲከበር ስላደረጋችሁ አመሰግናለሁ፡፡
በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች ይህ በዓል ያለአንዳች እክል በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በትጋትና በንቃት በየተመደባችሁበት ሃላፊነታችሁን በአግባቡ ስለተወጣችሁ አመሰግናለመሁ!!
አሁንም ቢሆን እንግዶቻችን ወደ አካባቢው በሰላም እስኪመለሱ ድረስ በተጀመረው የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት እስከመጨረሻው ድረስ በትጋት እና በቅንጅት መስራታችንን እንድንቀጥል እና በነገው እለት የሚከበረው የሆራ አርሰዴ በዓልም በሰላም እንዲጠናቀቅ ፣ ሁላችንም ይበልጥ ተጠናክረን በትብብርና በሃላፊነት ስሜት ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በድምቀት እንዲከበር ያደረጋችሁት ጥረት የደንብ መተላለፎች በመከላከሉ እና በመቆጣጠሩ ላይ መቀጠል አለበት።
በድጋሚ መልካም የኢሬቻ በዓል!
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments