
ባለስልጣኑ የሆራ ፊንፊኔ ማክበሪያ ቦታ ላይ ፅዳት አካሄደ።
ባለስልጣኑ የሆራ ፊንፊኔ ማክበሪያ ቦታ ላይ ፅዳት አካሄደ።
20/01/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 ሆራ ፊንፊኔ በዓል ማክበሪያ ቦታ የሆነውን የወንዝ ዳርቻ እንዲሁም የኢሬቻ ፓርክ ጊቢ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ኦፊሰሮች በጋራ በመሆን አፀዱ።
በቦታው ተገኝተን ያነጋገርናቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መአዛ እንዳሉት ባለስልጣኑ ከከተማ አስተዳደሩ ከተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት በተጨማሪ እንደነዚህ አይነት ተልእኮዎችን ተቀብሎ በሙሉ ተነሳሽነት እንደሚያከናውን ገልፀዋል።
አክለውም በክፍለ ከተማቸው የሚከበረውን ሆራ ፊንፊኔ ሲከበር ከውስጥም ከውጭም ሀገር ለሚመጡ የበዓሉ አክባሪዎች በእንግዳ ተቀባይነት ባህል ማስተናገድ እንዳለብን አስረድተዋል። በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም አካል የራሱን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments