
ባለስልጠኑ አዋኪ ድርጊቶችን በመከልከልና በስነ_ምግባር ብልሹ አሰራር ዙርያ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
ባለስልጠኑ አዋኪ ድርጊቶችን በመከልከልና በስነ_ምግባር ብልሹ አሰራር ዙርያ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
15/1/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣኑ ከጉለሌ ፣ አራዳ ልደታ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አዋኪ ድርጊቶችን በመከልከልና በስነ_ምግባር ብልሹ አሰራር ዙርያ በጉለሌ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
መደርኩ በሀገር ሽማግሌዎች ፣ በሀይማኖት አባቶች እና በሀዴ ስንቄዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የከተማዋን ደንብ ጥሰቶች በመከላከል በመቆጣጠር ከተማዋን ውብና ፅዱ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ምክትል ሰራ አስኪያጁ አዋኪ ድርጊቶች ትውልድን የሚጓዳ የትውልድ ጠንቅ በመሆናቸው የከተማው ነዋሪ ከባለስልጣኑ ጋር በመስራት በአካባቢው የሚገኙ አዋኪ ድርጊቶችን መከለከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ከተማችን ውስጥ የሚሰሩ በርካታ የልማት ስራዎች ቢኖሩም ብልሹ አሰራሮችም ስለሚኖሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሀዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የማድረግ ሰራዎች በመስራት ህብረተሰቡን የማንቃት ስራ መሰራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በአዋኪ ድርጊቶችን በመከላከለ ዙርያ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ አሰልጣኝ በሆኑት ዶ/ር ዋና ኢኒስፔክተር ኤርሚያስ ከበደ እና ''ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ለመከላከል የህብረተሰብ ሚና'' በሚል የተዘጋጀ ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ቀር ምክክር ተካሂዶበታል።
በሰነዱ የማህበረሰባዊ እሴቶች ምንነትና ጠቀሜታ፣ ከማህበረሰብ እሴቶች ስለማፈንገጥ፣ የማህበረሰብ ጠንቅ የሆነው አዋኪ ድርጊቶች በአዲስ አበባ ምን እነደሚመስል ፣ አዋኪ ድርጊቶችን እንዴት መፍታት እና መከላከል እንደሚቻልና ሙስና ስለሚያስከትለው ጉዳት ግንዛቤ ተፈጥሯል።
ስልጠናው በጣም ጠቃሚ በመሆኑ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መሰጠት እንደሚገባ እና የከተማው ነዋሪ ከባለስጣኑ ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት የውይይቱ ተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየታቸውን ተሰጥተዋል።
ዘገባው ፦ የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments