የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር...

image description
- In code inforcement    0

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ አስረከበ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ አስረከበ።

               15/ዐ1/2018 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ወረዳዎችን በማስተባበር በወረዳ 07 ያስገነባውን የአቅመ ደካማ ቤት በማጠናቀቅ የምርቃት መርሐ ግብር አካሄደ ።

የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የደንብ ማስከበር ከከተማ አስተዳደሩ የተሰጠዉን ተልዕኮ ከመወጣት ጎን ለጎን ሰው ተኮር ተግባር ላይ የሚያደርገው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ደንብ መተላለፎችንና ህገወጥ ተግባራትን ከመከላከል ባሻገር ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ችግር ፈቺ የሆኑ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በመስራት ለህብረተሰቡ ያለውን አለኝታነት በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶችን በማስተባበር ቀን ከለሊት በመስራት የቤት ግንባታውን በማጠናቀቅ ለባለቤቱ ማስረከባቸውን አስታውቀዋል።

ደንብ ማስከበር ህገወጥነትን ከመከላከል ጎን ለጎን ኦፊሰሩን በማስተባበር በሰው ተኮር ስራ ላይ በመሳተፍ ላከናወኑት የአቅመ ደካማ ቤት ማደስ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ የንፋስ ስልክ ላፍቶ የብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ገልጸዋል።

የቤት እድሳት የተደረገላቸው ወ/ሮ መሰረት ወንድሙ ከሀያ አመታት በላይ ለመኖር አመቺና ጽዱ ባለሆነ መኖርያ ቤት ውስጥ መኖራቸውን ጠቅሰው በተደረገላቸው በጎ ተግባር መደሰታቸውንና ምቹና ዘመናዊ መኖሪያ እንዳጋኙ በመግለፅ ምሳጋናቸው አቅርበዋል።

በእለቱ የቤት ግንባታው ሲከናወን ድጋፍ ላደረጉ እና ለአስተባበሩ አካላት የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments