
ባለስልጣኑ አዋኪ ድርጊት እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ዕቅድ መርሀ ግብር ላይ ውይይት አካሄደ።
ባለስልጣኑ አዋኪ ድርጊት እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ዕቅድ መርሀ ግብር ላይ ውይይት አካሄደ።
15/01/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት አዋኪ ድርጊት እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በቀጣይ ለሚያካሂደው የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ዕቅድ መርሀ ግብር እና የነሀሴ ወር የክፍለ ከተሞች ድጋፍና ክትትል ሪፖርት ላይ ከክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት አካሂድዋል።
በመድረኩ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በአዋኪ ድርጊት መከላከል ላይ በደንብ ቁጥር 150/2015 እና ፀረ-ሙስና እና ብልሹ አሰራር መከላከል ዙሪያ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ዕቅድ የድርጊት መርሀ-ግብር እንዲሁም የነሀሴ ወር የክፍለ ከተሞች ድጋፍና ክትትል አጭር ሪፖርት በማቅረብ ውይይት ተካሂድዋል።
ከአዋኪ ድርጊት ጋር ተያይዞ በሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮች ከመከላከል አኳያ የንቅናቄ መድረክ መዘጋጀቱ ህብረተሰቡ ላይ በቅርበት ግንዛቤ ከመፍጠርና ብልሹ ተግባራቱን ከመከለከል አንፃር ጉልህ ሚና እንዳለው በማንሳት በቀረቡት ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የባለሥልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በመድረኩ ላይ በመገኘት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ የተጣለበትን ኃላፊነት የመወጣት ተግባሩን በህብረተሰቡ ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ እነዚህ ዓይነት የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ማህበረሰቡን የማንቃት ስራዎችን መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የሚደረጉ የንቅናቄ መድረኮችን ከዚ ቀደም ከሚሰጡበት በተለየ መልኩ ወቅቱ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም ተደራሽ የማድረግ ተግባራት የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments