ባለስልጣኑ የተገልጋይ መማክርት ካውንስል ምስረታ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የተገልጋይ መማክርት ካውንስል ምስረታ።

ባለስልጣኑ የተገልጋይ መማክርት ካውንስል ምስረታ።

                    9/01/2018ዓ.ም
                      አዲስ  አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት የተገልጋይ መማክርት ካውንስል ምስረታ እና ከተቋሙ ጋር በቅንጅት ከሚሰሩ የሲቪል ማህበራት ጋር የትስስር ሰነድ ፊርማ የባለስልጣኑ ኃላፊዎች እና የሲቪል ማህበራት በተገኙበት ተካሂዷል።

በዕለቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በዛሬው ዕለት በምናደርገው የመማክርት ጉባዔ ምስረታ ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተግባር እና ኃላፊነት እንዲሁም የተሻለች ከተማ ለመገንባትና የምናገለግለውን ህዝብ ደስተኛ ለማድረግ ከእናንተ ጋር በጋራ የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

የተገልጋይ መማክርት ካውንስል ምስረታ ሰነድ እና ከባለስልጣኑ ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ሲቪል ማህበራት ጋር የትስስር ሰነድ ያቀረቡት የተቋሙ የስ/ዝ/አ/አ/ክ/ድ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀፀላ  እንዳሉት የካውንስል ምስረታው ተቋሙ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ ከተገልጋዬች ጋር በጋራ ለመስራት እድል የሚፈጥር እና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምን ነው ብለው ለካውንስሉም 7 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የጠቅላላ ጉባዔው አባላት ምርጫ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ጠቅላላ ጉባዔው 46 አባላት ሲኖረው 22 አባላት ከተገልጋይ ፣14 ከሲቪል ማህበራት  ቀሪዎች ከተቋሙ እና ከባለስልጣኑ ጋር በጋራ ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በመምረጥ የተገልጋይ መማክርት ካውንስል በባለስልጣኑ ተመስርቷል።

በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ በጋራ ለመስራት ከሲቪል ማህበራት ጋር የስምምነት ሰነድ በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments