በግጭት አፈታት እና በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠ...

image description
- In code inforcement    0

በግጭት አፈታት እና በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።

በግጭት አፈታት እና በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።

                           8/01/2018
                            **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለማዕከልና ለክፍለ ከተማ  እና የማዕከል ሰራተኞች በግጭት አስተዳደር  አፈታት እና የውሳኔ አሰጣጥ  ዙርያ በባለስልጣኑ  መሰብሰቢያ አዳራሽ  ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጠኑ  የስልጠና ጥናት  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ ስልጠና አቅም የሚገነባበት  በመሆኑ ሰለጣኞች በትኩረት በመከታታል እንዳለባቸው አቅጣጫ በመስጠት  ስልጠናውን አስጀምረዋል።

ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ  በሆኑት አቶ ወልደመድህን መኮነን የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው በዋናነት ስለ ግጭት አፈታት ፅንሰ ሀሳብ፣ ስለ ግጭት አይነቶች ፣ስለ የግጭት መንስኤዎች፣ ግጭት አፈታት ዘዴዎች ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የውሳኔ አሰጣጥ አይነቶች  ዙሪያ ላይ በማተኮር ካለው የባለስልጣኑ ነባራዊ የስራ ባህል ጋር በማገናኘት ስልጠናው ተሰጥቷል።

ሰልጣኞችም በወሰዱት ስልጠና  ግጭቶች እንዴት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ እና እንዴት በአስተዳደር ሁኔታዎች መፈታት እንዳለበት በቂ ግንዛቤ እንደተፈጠረላቸው   የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተገኝተው ስልጠናውን ወደ ተግባር በመቀየር በእለት ተእለት ስራዎች ላይ መጠቀምና  ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

መረጃው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments