
ባለስልጣኑ የጎቤ እና የሺኖዬ በዓልን በደማቅ አከበረ
ባለስልጣኑ የጎቤ እና የሺኖዬ በዓልን በደማቅ አከበረ
መስከረም 05/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የጎቤ እና ሺኖዬ በዓልን ከበዓሉ ታዳሚ እንግዶች በማሳተፍ በደማቅ አከባበርና በልዩ ዝግጅት ከባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች ጋራ አክብሯል።
በዕለቱ የባለስልጣኑ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ወጣቶቹ የኦሮሞን ባህል ለማስተዋወቅ የሰሩትን ስራ አድንቀው ይህ ባህል ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ባህላዊ ጨዋታ ተሳታፊዎች ሺኖዬ (Shinooyyee)እና ጎቤ (Goobee) በገዳ ሥርዓት ውስጥ ከሚከወኑ የዘመን መለወጫ ባህላዊ ትውፊቶች መካከል የሚካተቱ በመሆናቸውን ገልፀው የደንብ መተላለፎቸ ለመከላከል አጋዥ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።
ሺኖዬ (Shinooyyee)በልጃገረዶች (ቀሬዎች) የሚከወን ሲሆን ጎቤ (Goobee)ደግሞ በወጣት ወንዶች (ቄሮዎች) የሚከወን ባህላዊ ጨዋታ ናቸው።
ባህላዊ ትውፊቶቹ የዘመን መለወጫን የሚያበስሩ ሲሆኑ ወጣቶቹ ያለፈውን ከማመስገን ባለፈ የፊቱን ብሩህ ዘመን መሻታቸውን የሚገልጹባቸውም መሆኑ ገልፀዋል።
በልጃገረዶች (ቀሬዎች) የሚከወነው ሺኖዬ(Shinooyyee) ጨዋታ እንደየአካባቢዎቹ ‘ቁኒ ቡቅፈና’፣ ‘ቃሜ’፣ ‘እንግጫ’ እና የተለያዩ መጠሪያዎች አሉት።
ጎቤም በተመሳሳይ በወጣት ወንዶች (ቄሮዎች)በየሰው ቤት እየተዞረ ከሳምንት በላይ የሚጨፈር ባህላዊ የዘመን መለወጫ ብስራት መሆኑ የበዓሉ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
መረጃው፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments