
ባለስልጣኑ በንብረት አያያዝ፣ አወጋገድና ደረሰኝ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ በንብረት አያያዝ፣ አወጋገድና ደረሰኝ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
05/ዐ1/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንብረት አያያዝ፣ አወጋገድና ደረሰኝ አጠቃቀም ዙርያ ከማእከል እስከ ወረዳ ለተውጣጡ የፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ የስልጠና እና ጥናት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ ስልጠናው ከደንብ ተላላፊዎች የሚወረሱ ንብረቶች በአግባቡ እንዲወገዱ ባለሙያዎች ላይ አወንታዊ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
የስልጠናው ዋና አላማ ተገቢው አሰራር እና መመሪያ ተጠብቆ ንብረቶች በአግባቡ እንዲያዙና እንዲወገዱ ለማስቻል ነው ሲሉ ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የኦዲት እና ኢንፔክሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ መአዛ አበበ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በመጨረሻም ከስልጠናው ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።
ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments