
በህብረት ችለናል ! ባለስልጣኑ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቁን አስመልክቶ የፓነል ውይይት መድረክ አካሄደ
በህብረት ችለናል !
ባለስልጣኑ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቁን አስመልክቶ የፓነል ውይይት መድረክ አካሄደ
05-ዐ1 -2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን " የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ነው " በሚል መሪ ቃል የህዳሴ ግድብ ምረቃ በተመለከተ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በወርቃማ ሰኞ ፕሮግራም ላይ ከመላው የማዕከል ሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በትውልልድ ቅብብሎሽ የተገነባ ኢትዮጵያዊያን ታሪክ መስራት እንደሚችሉ ለዓለም ያሳዩበት ድንቅ ፕሮጀክት ነዉ ሲሉ ገልጸዋል ።
ህዳሴ ግድቡ በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በመቋቋም በራሳችን ባለሙያዎችና በራችሳችን ገንዘብ በመገንባት ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ሀያልነቷን ያሳየችበት መጭው ትውልድ የሚኮራበት ድል ነው ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።
ለመወያያ የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ቀርቧል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ የግድቡ አንድምታዎችን ለሀገሪቱ ህዳሴ ፣ ለተፋሰሱ እና ቀጠናዊ ትስስር እንዲሁም ለአፍሪካ ትንሳኤ የሚኖረውን ሚና ከሰራተኛው ጋር ውይይት አድርጓል።
የግድቡ መጠናቀቅ ሀገራዊ መነቃቃትና ህዝባዊ ተሳትፎ ለሌሎችም ሀገራዊ ልማቶች የጋራ መግባባት በመፍጠር ማስቀጠል እንደሚገባ በሰነዱ ተገልጿል ።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው መላው ኢትዮጽያዊን በአንድነት ተደጋግፈው የሰሩትን ዘመን ተሻጋሪ ሀገራዊ ፕሮጀክት የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገንባት ማጠናቀቅ በመቻላችን እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በመጨረሻም በሰነዱ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments