ባለስልጣኑ በዛሬው ኅብር ቀን በነፍስ ስልክ ላፍ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በዛሬው ኅብር ቀን በነፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ

ባለስልጣኑ በዛሬው ኅብር ቀን በነፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ

         ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም
          ** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ  የኅብር ቀን በማስመልከት ለነዋሪዎች፣ለሚያሳድጋቸው ልጆችና  እና ለሰራተኞቹ ማዕድ አጋርቷል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት ረዳት የሌላቸው ወገኖቻችን ለመደገፍ መንግስት በርካታ ስራዎች መስራቱ ገልፀው በየአካባቢአችን ረዳት የሌላቸው ወገኖቻችን አቅምን በፈቀደ መልኩ መደገፍ እንዳለብን አሳስበዋል፡፡

በፕሮግራሙ የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት  ሃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ በክረምቱ ወራት ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካምችን፣ የሀገር ባለውለታዎችንና በዝቀተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የህብረተስብ ክፍሎችን ቤት በማደስና ማዕድ በማጋራት ሲደግፋ መቆየታቸው ገልፀው አሁን ልበቀናዎችን በማስተባበር የበዓል ስጦታ ማዘጋጀታቸው ገልፀዋል።

የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በመደጋገፍ ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ወገኖቻችን የምናደርገውን ድጋፍ ማጠናከር ይገባናል  ድጋፍ ላደረጉ ልበቀናዎች ምስጋና አቅርበዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments