ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2...

image description
- In code inforcement    0

ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር አካሄደ

ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር አካሄደ

                ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም
                 ** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የተሻለ ዕቅድ አፈጻጸምላስመዘገቡ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች፣ባለድርሻ አካላትና ሰራተኞች የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በክ/ከ አዳራሽ በዛሬው እለት አካሄደ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሙ ሙሄ ፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን መሀመድ እና ሌሎችም የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በእውቅናና ምስጋና መርሀግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል በመቆጣጠር በማስተማር ለህብረተሰቡ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑ ገልጸዋል

አክለውም  በቀጣይ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየደረጃው የተሰማራው ሰራተኛና ኦፊሰሮች የተጀመረው ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሰፊ ስራ በቀጣይም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብሩ የመክፈቻ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ተግባራትን በመከወን ህገወጥ ግንባታ 15%፣ህገወጥ ቆሻሻ አወጋገድ 70%፣ አዋኪ ድርጊት 4.7 ጨምሮ በጥቅሉ በክ/ከተማው 52.1% የደንብ ጥሰትን በመቀነስ አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት ዓመትመሆኑ ተናግረዋል።

ኃላፊው በቀጣይ 2018 ዓ.ም የተለያዩ የከተማ አስተዳደሩ የጣለብንን ኃላፊነት ንቁ የሆነው የህብረተሰቡ አብሮነት ቀጣይነት እንዲኖረው አንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በእለቱ በበጀት ዓመቱ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በተቋሙ ጉልህ ተሳትፎ ለነበራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጽ/ቤቱ ምረጥ ፈጻሚ ባለሙያዎች ፣ ሴክተር ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የጎልደን እና የአረንጓዴ ልዩ ተሸላሚ የሆኑ ወረዳዎች የምስጋና ሰርተፍኬትና እውቅና የመስጠት መርሀግብር ተከናውኗል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሙ ሙሄ በ2017 በጽ/ቤቱ የመጡት ለውጦች በቀጣይ አመትም በበለጠ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በመግለጽ በቀጣይ በጋራ እንደሚሰሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments