ባለስልጣኑ በደንብ ማስከበር የመልካም አስተዳደር...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በደንብ ማስከበር የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ቀጣይ በሚሰራቸው ተግባሮች ዙርያ ከነዋሪዎች ጋር ፊት ለፊት ውይይት እያካሄደ ነው

ባለስልጣኑ በደንብ ማስከበር የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ቀጣይ በሚሰራቸው ተግባሮች ዙርያ ከነዋሪዎች ጋር ፊት ለፊት ውይይት እያካሄደ ነው  
      
          23/ 11/2017 ዓ.ም
         ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 እቅድ አፈጻጸም ፣ የ2018 እቅድ ውይይት እና በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ከከተማው ነዋሪዎች ጋር የፊት ለፊት ውይይት መድረክ በአድዋ ሙዚየም የስብሰባ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል ። 

መድረኩ በደማቅ ሁኔታ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር፣በሀይማኖት አባቶች በሀገር ሽማግሌዎች አባ ገዳዎች ምርቃት ተጀምሯል።

በመድረኩ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ  ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ  የአገልግሎት  አሰጣጥና አውት ሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ  አቶ በቀለ ተመስገን ፣ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ከማዕከል አስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ፣ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ እና ከ119 ወረዳዎች  ከተወጣጡ የከተማው ነዋሪዎች፣ የህብረተሰብ ተወካዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል ። 
 
አጠቃላይ ዝርዝር መረጃው መድረኩ እንደተጠናቀቀ ይዘን የምንመለስ ይሆናል። 

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments