ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡን ቀ...

image description
- In code inforcement    0

ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

                20/ 11/2017 ዓ.ም
              **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  "የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት አገልግሎት አሰጣጣችንን ምቹ ቀልጣፋ እና ፍትሀዊ እናደርጋለን" በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማዎች የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል ።

በመድረኮቹ የክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ለህብረተሰቡ ለውይይት መነሻ እንዲሆን  ቀርቧል።

የህዝብ ንቅናቄ ማድረግ አስፈላጊነቱ ባለስልጣኑ በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተግባር እና ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ለመፈፀም በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከከተማው ህብረተሰቦች ጋር በሚደረጉ በህዝብ ንቅናቄ መድረኮች በመለየት እና ችግሮችን በእቅድ ለመፍታት እንደሆነ ተገልጿል ፡፡

በመድረኩ በ2017 በጀት ዓመት ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣትና በርካታ ሰው ተኮር ሰራዎች በመስራት ያስመዘገብነውን ድል በላቀ ደረጃ ለማሰቀጠልና በ2018 የያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ እንዲሁም ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ገልጸዋል ፡፡

የምናገለግለው የህብረተሰብ ክፍል በተቋማችን ከአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያና የተፈቱበት አግባቦችን በጋራ በመምከር በቀጣይ መፈታት የሚገባቸውን ችግሮች ለመለየትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መድረኩ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል ፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅና የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከል ከደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments