"ሙስና ስጋት የማይሆንባት ደንብ ማስከበር ባለስ...

image description
- In code inforcement    0

"ሙስና ስጋት የማይሆንባት ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እንፍጠር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ ተካሄደ

"ሙስና ስጋት የማይሆንባት ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እንፍጠር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ ተካሄደ

             16/ 11/2017 ዓ.ም
              **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከ11 ክ/ከተማ እና ከ119 ወረዳዎች ለተመለመሉ ተባባሪ አካላት/Focal person/ በ2018 እቅድ እና በቀጣይ ትኩረት በማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ የውይይት መድረከ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት በመፈጸም በከተማችን የደንብ ጥሰት እንዲቀንስ በማድረግ ሂደት ውስጥ የስነምግባር ብልሹ አሰራር እንዳይፈጸም ተባባሪ አካላት በአግባቡ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ ውጤታማ ተግበር ለማከናወን ውይይቱ አስፈለጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

የስነ ምግባር ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተዋቀሩ ተባባሪ አካላት /Focal person/ የ2018 ዓ.ም እቅድ እና የመወያያ ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ቀርቧል።

በሰነዱ የ2017 አፈጻጸም ፣ የ2018 በጀት ዓመት ግቦችና ዝርዝር ተግባራት፣ በየደረጃው ያሉ ተባባሪ አካላት ሊያተኩሩባቸው የሚገቡ የስነምግባር ችግሮችን የመፍታት እና ሙስና እንዴት መከላከል እንደሚቻል  ማከናወን የሚገባቸው ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል።

የውይይቱ ዓላማ ከክ/ከተማና ከወረዳ የተወጣጡ ተባባሪ አካላት በየደረጃው ያለው መዋቅር ውስጥ የስነ ምግባርና ብልሹ አሰራር እንዳይከሰት ቀድሞ ለመከላከል መሆኑን አቶ እዮብ ገልፀዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ብልሹ አሰራርን ለመታገልና በስነ ምግባር የታነጸ ኦፊሰር ለመገንባት የበኩላቸውን በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments