የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህብረተ...

image description
- In code inforcement    0

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ

             13- 11- 2017 ዓ.ም
              **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሁሉም ወረዳዎች " የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የአገልግሎት አሰጣጣ ምቹ፣ ቀልጣፋ ፍትሀዊ እናደርጋለን" በሚል መሪ ቃል የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ ።

በተደረጉት የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ላይ በመዘዋወር ምልከታ ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ህገ-ወጥነትን ለማስቀረት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሰላም ባለቤት በማድረግ እና ህገ-ወጦችን መከላከል ፣ መቆጠጠርና በጋራ እርምጃ መዉሰድ ሲቻል መሆኑን ገልፀው በቅንጅት መስራት በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ሲሉም ገልጸዋል ።

በ2017 በጀት ዓመት የደንብ ጥሰቶችን ከመከላከል አንጻር ሰፊ ስራ መሰራቱንና ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከል፣ሰፊ የግንዛቤ ስራዎችን በመስራትና የደንብ ጥሰት የፈጸሙ አካላትን ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድና በመቅጣት አመርቂ ውጤት  መገኘት መቻሉን ይህን ውጤት  በ2018 በጀት ዓመት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ክፍተቶችን በማረም በትኩረት እንደሚሰሩ በየወረዳዉ ያሉ አመራሮች ሀሳባቸዉን ገልጸዋል፡፡

ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ በመድረኮቹ ተገልጿል ።

በመድረኩ በየወረዳዎቹ የሚገኙ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ቀርቧል ።

የባለስልጣኑ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በክላስተር በመከፋፈል ወረዳዎችን በቦታው በመገኘት የህዝብ ንቅናቄው መድረክ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ አድርገዋል ።

በቀረቡት ሪፖርትና ሰነድ ላይ ከህብረተሰቡ፣ ከጸጥታ አካላት፣ከብሎክ አደረጃጀቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግየተነሱ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበቷል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments