ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

               12- 12- 2017 ዓ.ም
              ** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ መግቢያ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ፕሮግራም ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር አካሂዳል፡፡

በዕለቱ ንግግር ያደረጉት  የባለስልጣኑ የስነምግባርና የጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬእተር እንደገለፁት በሳምንቱ ያሉትን የስራ ጊዜያቶች በንቃት ለማሳለፍና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተቀራርቦ ለመስራት ፕሮግራሙ የሚያግዝ ነው በማለት የመልካም ሳምንት ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የህግ ቡድን መሪ አቶ ብርሃኑ ኮርሳ የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ ለሰራተኞች ልምድና እውቀት ይሆን ዘንድ አካፍለዋል ።

በተጨማሪም የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ ያዘጋጁትን ሰነድ ለሰራተኛው በሚመጥን መልኩ በዝርዝር አቅርበዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments