በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት...

image description
- In code inforcement    0

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ ቁልፍ አስረከበ

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ ቁልፍ አስረከበ

               09/12/ 2017 ዓ.ም
                  አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በክረምት በጎ ፍቃድ ስራ በወረዳ 02 ያስገነባውን የአቅመ ደካማ ቤት በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክቧል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ደንብ ማስከበር በከተማችን የሚስተዋሉ ደንብ መተላለፎችንና ህገ-ወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎን ለጎን ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ችግር ፈቺ የሆኑ ሰው ተኮር የበጎፍቃድ ስራዎችን በመስራት የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣የማዕድ ማጋራትና የቤት ዕድሳት ተግባራትን በማከናወን ለህብረተሰቡ ያለውን አለኝታነቱ በተግባር  እያረጋገጠ መሆኑ ገልጸዋል ።

አክለውም የተጀመረው ሰው ተኮር በጎ ተግባር በቀጣይም  በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ  እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

በመርሐ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አቶ አበራ ኢቲቻ  በክረምት የዘጠና ቀናት ዕቅድ 2 ቤቶችን ለመገንባትና ለማደስ ታቅዶ በዛሬው ዕለት አንዱን ቤት በራስ አቅም  ኦፊሰሮችን ባለሀብቶችን በማስተባበር ከፈረሳ ጀምሮ እስከሚጠናቀቅ በየጊዜው ክትትል በማድረግና ሁሉም አካል የበኩሉን ሚና በመወጣት 1.3 ሚሊዩን ብር በላይ ወጪ ተደረጎበት ለምረቃ መብቃቱን ገልጸዋል ።

የቤት እድሳት የተደረገላቸው ወ/ሮ ውዴ ያኢ በተደረገላቸው በጎ ተግባር መደሰታቸውን በመግለፅ በተግባሩ ለተሳተፉ በሙሉ ላቅ ያለ ምሳጋቸውን አቅርበዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ፣የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አቶ አበራ ኢቲቻ ፣ የክ/ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ኤርሚሾ ፣ የወረዳ 02 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዱኛ ዘነበ ፣የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ኦፊሰሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የቤት ግንባታው ሲከናወን ድጋፍ ላደረጉ እና ለአስተባበሩ አካላት የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments