የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኦፊሰሮች ከሰላም ሰራዊት...

image description
- In code inforcement    0

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኦፊሰሮች ከሰላም ሰራዊት አባላትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት የህገወጥ መከላከልና የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኦፊሰሮች ከሰላም ሰራዊት አባላትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት የህገወጥ መከላከልና የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ

8/12/ 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እና ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት "እኔ ለከተማዬ ሰላም ባለቤት እና ጠባቂ እሆናለሁ" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት ህገወጥነት የመከላከልና የፀጥታ ስምሪት የመስጠት ፕሮግራም በአበበ በቂላ ስታዲየም አካሂደዋል ።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ ከ/ ክፍለ ከተማ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ክ/ ከተማችን ከሁሉም የከተማችን አካባቢ እና ከመላው የሀገራችን ክልሎች የተወጣጡ ማህበረሰብና ሸማቾች አንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰፊ ግብይት  የሚፈጽሙበት እንደመሆኑ በተደራጀ የፀጥታ ስምሪትና  ዲሲፒሊን አስተማማኝ ሰላሟ የሰፈነ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ጠንክረን መሥራት ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የክፍለ ከተማችን የፀጥታ አካላት ፣የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና የሰላም ሠራዊት ሰላምና ፀጥታን እንዲሰፍን በቅንጅት በመስራታቸው ህብረተሰቡ በሰላም ወቶ እንዲገባ እንዲሰራና የፈለገውን እንዲገበያይ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ።
በቀጣይም ለሚከበሩት ሀይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም ተከብረው እንዲጠነቀቁ ሁሉም አካላት የቅንጅት ስራቸውን በማጠናከር የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments